Jan 31, 2025 .
የኢትዮጵያ እና ጃፓን የንግድና ኢንቨስትመንት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል

የኢትዮጵያ እና ጃፓን የንግድና ኢንቨስትመንት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡
የኢትዮጵያ እና ጃፓን የንግድና ኢንቨስትመንት እያደገ መምጣቱን በመክፈቻ ንግግራቸው የገለጹት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ ይህ ሲምፖዚየም በተለያዩ ዘርፎች ያሉትን እድሎች ለመጠቀምና አብሮ ለመስራት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ሲሆን ምክር ቤቱም የሁለቱን ሀገራት የቢዝነስ ትስስር ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
ሁለተኛ ቀኑን በያዘው በዚህ ሲምፖዚየም የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር እንደገና አበበ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ፣ በጃፓን፣ ማይንማርና ላኦስ የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ዳባ ደበሌ፣ የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሞቱማ ተመስገን እንዲሁም የጃፓንና የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ተወካዮች ታድመዋል፡፡

