Read more

Jan 31, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው 3ኛው የፀረ ህገወጥ ንግድ ጉባኤ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው 3ኛው የፀረ ህገ ወጥ ንግድ ( 3rd National Anti-illicit Trade Summit) ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ጉባኤ በተለይም በቡና ወጭ ንግድ፣ በቁም እንስሣት የወጭ ንግድ እንዲሁም በፋርማሲውቲካልና በጠረፍ አካባቢ በሚካሄድ የህገ ወጥ ንግድ እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

በመድረኩ ላይም የኢፌዴሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሣሁን ጎፌን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላት፣ የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች፣ በዘርፉ ላይ የተሠማሩ  ባለድርሻ አካላት እና ሌሎች ተዋናዮች ተገኝተዋል።

ህገ ወጥ ንግድ የሀገርን ኢኮኖሚ በመጉዳት ትልቁ እንቅፋት መሆኑን የተናገሩት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ዶክተር ካሣሁን ጎፌ ችግሩ ህጋዊ ነጋዴውን ከመጉዳት ባሻገር የሀገርን ሀብት ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲሸሽ የሚያደርግ መሆኑን በመድረኩ ላይ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸው ምክር ቤቱ ህጋዊ የንግድ ሥርአት እንዲሠፍን ለማሥቻል እና ህገ ወጥ ንግድ እንቅስቃሴ ለመከላከል በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸል።

በጉባኤውም በተለዩ ዘርፎች የህገ ወጥ ንግድ እንቅሥቃሴ እና መፍትሄዎቻቸው ላይ ጥናቶች የሚቀርቡ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ይደረግባቸዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia