Read more

Jan 31, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ከህንድ ኤምባሲ ተወካይ ጋር ተወያዩ፡፡

ዋና ጸሐፊው በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ ሁለተኛ ጸሐፊ/የንግድ አታሼ ራቪ ሻንከር ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ተወያይተዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመን እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግና በተለያዩ ዘርፎች የሚሰማሩ የህንድ ባለሀብቶች የሚያጋጥሟቸውን እንቅፋቶች ለመፍታት በመቀራረብ መስራት እንደሚገባና ለዚህም ቁርጠኛ መሆናቸውን ሁለቱ ወገኖች ገልጸዋል፡፡ 

ዋና ጸሐፊው በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉን ጨምሮ በተከናወኑ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርም ስራዎች በርካታ ዘርፎች ለህንድ ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንደምትሆንና ያሉትን መልካም እድሎች አብራርተውላቸዋል፡፡

የህንድ ኩባንያዎች በአይ ሲ ቲ፣ በቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በማምረቻና በሌሎችም መስኮች የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ሚስተር ራቪ ሻንከር ጠቁመዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia